
ቤተስዳ ሜሪላንድ
ጤና ይስጥልኝ!
እርስዎን እንግሊሽ ናውን ሳስተዋዉቆት በአስተማሪዎቻችን፡ በተማሪዎቻችን እና በሰራተኞቻችንን ስም የእኛን ሞቅ ያለ አቀባበል ስገልጽ በደስታ ነዉ፡፡
በተለያዩ ሀገራት በመኖር ጥናት ማድረግ እጅግ አስገራሚ ተሞክሮ ሊሆን ይችላል፡፡ በተለያዩ አጋጣሚዎች አዳዲስ ሰዎችን ያገኛሉ፤ ስለ ሌሎች ባህሎች ያውቃሉ፤ እንዲሁም ዓለምን በየቀኑ በተለየ መንገድ ይመለከቷታል፡፡ ይሁን እንጂ እንደ ሕይወት ተሞክሮዎ በውጭ አገር ሲኖሩ ለረጅም ወይም ለአጭር ጊዜ ሌላ ቋንቋ መናገር እርስዎን ሙሉ ያደርጎታል፤ እንዲሁም በአካባቢዎና እና በዓለም ላይ ለሚኖሩ ሰዎች በበለጠ አስተዋፅዖ እንዲያደርጉ ያስችሎታል፡፡
ይህንን ግንዛቤ ዉስጥ በማስገባት እንኳን ወደ እንግሊሽ ናው በደህና መጡ! ይህ ትምህርት ቤት የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታዎ ከሚገምቱት በላይ በፍጥነት የሚሻሻልበት ቦታ እንዲሆን እንፈልጋለን፡፡ እኛ ጋር ሲማሩ በትጋት እንዲሰሩ እንጋብዝዎታለን፤ ነገር ግን እንዲህ በማድረግዎ ብቃት ባላቸዉ መምህራን እና አስተዳደራዊ ሰራተኞቻችን ድጋፍ እና እንክብካቤ እንደማይለየዎት ጥርጥር የለውም፡፡
እንግሊሽ ናው! ባለብዙ ገፅታና ጠቃሚ ታሪኮች አሉት፦
- ከፍ ያለ ዕዉቀት፡ እንግሊሽ ናው! ከፍተኛ የቋንቋ ትምህርት ይሰጣል፤ ክፍሎቻችን በአነስተኛ ቡድን የተዋቀሩ ናቸዉ፡፡ በእያንዳንዱ ክፍል ከስድስት የማይበልጡ ተማሪዎች ይማራሉ፡፡ ይህ አነስተኛ የክፍል አደረጃጀት ለተማሪዎቻችን የተሟላ መማሪያ እና እንዲሁም ጠንካራ ግንኙነቶችን ለማዳበር እድል ይሰጣቸዋል፡፡. ከዚህም በላይ መምህራኖቻችን እንደ ተማሪዎቻችን ሁሉ አነስተኛ የቡድን አወቃቀር ይወዳሉ፡፡ይህም በዋሽንግተን ዲሲ ክልል ውስጥ የሚገኙትን ከፍተኛ የESL መምህራንን ለመሳብ እና ለመያዝ አስችሎናል፡፡
- የተለየ ቦታ፡ እንግሊሽ ናው! የሚገኘው ከዋሽንግተን ዲሲ ጥቂት ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ በቤተስዳ፤ ሜሪላንድ ነው፡፡አካባቢው ደማቅ የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ መዳረሻ ሲሆን ባለፉት ሶስት ዓመታት ብቻ ከ 85 ሀገራት በላይ ተማሪዎችን ለማስተማር አስችሎናል፡፡ ጥቂት የዓለም ከተሞች ለዓለም አቀፋዊ ንግግር እንዲህ አይነት ማዕከላት ናቸው፤ ይህም ት / ቤቱን እንግሊዝኛ ለመማር እና አስደሳች የሆኑ ሰዎችን ለመተዋወቅ ጥሩ ቦታ እንዲሆን አድርጎታል፡፡
- ልዩ ቦታ፡ እንግሊሽ ናው! አቀራረቡ ለየት ያለና ሞቅ ባለ አቀባበል ያስተናግዶታል፡፡ እንደ ብዙዎቹ የቋንቋ ትምህርት ቤቶች እንግሊሽ ናው! ትልቅ ኩባንያ ወይም ፍራንቻይዝድ አይደለም፡፡ እዚህ ትምህርት ቤት እግሮ ከረገጠበት ጊዜ ጀምሮ ለእያንዳንዱ ተማሪዎች በምናደርገዉ እንከብካቤ ይረካሉ፡፡
በእስያ እና በአውሮፓ በተለያዩ ሀገሮች የመኖር እና የተለያዩ ቋንቋዎችን ለመማር እድል አግኝቻለሁ፤ ይህም ተሞክሮዬ ምን ያህል አስደሳች አሊያም ያልተሳካ ሊሆን እንደሚችልም በሚገባ ጠንቅቄ አውቃለሁ፡፡ ሆኖም እንግሊሽ ናው! ከፍተኛ ጥራት ያለው የእንግሊዘኛ ቋንቋ ክህሎት እንዲኖሮት በእንክብካቤ እና በእውቀት የታገዘ በህይወትዎ ውስጥ የበለጠ እና የተሻለ ስኬታማ ለመሆን የሚያነሳሳዎትን የንግግር ዘይቤ (ማለትም በእንግሊዝኛ) እንደሚያገኙ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
ተማሪዎቻችን ቋንቋን ለማወቅ ያላቸዉን ፍላጎት ለማሳካት እና በዛ ሂደት ውስጥ ለመደገፍ አብረን በመስራታችን ያስደስተናል፡፡ በግል ወይም በቡድን መጥተዉ እኛ ጋር እንደሚማሩ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
ትምህርትዎን የበለጠ ስኬታማ ለማድረግ የምንችለው ተጨማሪ ነገር ካለ እባክዎ ያሳውቁኝ፡፡
“ከልዩ አክብሮት ጋር”
ፖል ቦ
ፖል ቦስን
ዋና ስራ አስፈፃሚ
እንግሊሽ ናው!
ስልክ ቁጥር: +1 301 718 3575
ሞባይል: +1 703 785 4580